አቤ ጉበኛ

  1. home
  2. Author
  3. አቤ ጉበኛ
አቤ ጉበኛ

2 Published Booksአቤ ጉበኛ

አቤ ጉበኛ የመጀመሪያ ሥራቸው በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሲሆን ቀጥሎም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተቀጥረው በመንግሥት ሥራ ለስድስት ዓመታት ያህል ካገለገሉ በኋላ ሕይወታቸውን በአብዛኛው የገፉት በደራሲነት ነው።

አቤ ጉበኛ አጫጭር እና እረጃጅም ልቦለዶችን፣ ተውኔቶችን፣ ግጥሞችን እና ወጎችን ይጽፉ የነበረ ሲሆን ጭብጦቹም እንደ ጭቆና፣ ሙስና፣ መሀይምነት እና ማህበራዊ ኑሮ ላይ ያተኮሩ ነበር:: በመሆኑም በግዜው ከነበሩት ባለስልጣናት ጋር ተቃውሞም ፈጥሮባቸው እስከ እስር ደረጃ ደርሰው ነበር::

ደራሲ አቤ ወደ 20 መጸሃፎችን ያሳተሙ ሲሆን የ1966 “አልወለድም” በቀዳሚነት የሚጠቀስ ስራቸው ነበር:: “አንድ ለናቱ” የሚባለው ታሪካዊ ልቦለድ ስራቸው ደሞ በቴዎድሮስ ዙሪያ ሆኖ የዘመነ መሣፍንትንም የእርስ በእርስ ውጊያ የሚያሳይ በጥናት ላይ የተደገፈ ታላቅ ጽሁፍ ነው::

ደራሲ አቤ በወቅቱ የሰዓት እላፊ በነበረበት ወቅት በሌሊት ሲንቀሳቀሱ በጥይት ተመተው ጥር 30 ቀን 1972 ዓ.ም. ህይወታቸው እንዳለፈ ይነገራል::

Popular Books by አቤ ጉበኛ